ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች።
ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች።
<<የኔ ጣፋጭ አንዱን ለኔ ለእናትሽ ትሰጪኛለሽ?>> ስትል በትህትና ትጠይቃታለች።
ልጅም ትኩር ብላ ከተመለከተቻት በኋላ አንዱን አፕል ግምጥ አደረገችው...ቀጠለችና ሁለተኛውንም ደገመችው።
እናት በልጇ ሁኔታ ደንግጣ ፍዝዝ ብላ ቀረች።
ስሜቷን በቁጣ ልታሳያት ብትሞክርም ድንጋጤው ከለከላት።
እንዴት በኔ በእናቷ ትጨክናለች? ብላ አሰበች።
በዚህ መሃል የገመጠችውን አንዱን ለእናቷ እያቀበለቻት << እንኪ ማሚ ይበልጥ የሚጣፍጠውን ላንቺ>>> አለቻት። እናት ያልጠበቀችውን ክስተት በማየቷ ልጇን አቅፋ ተንሰቅስቃ አለቀሰች።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ቢያንስ በእያንዳንዳችን ዙርያ እኛ ምንም ሳናውቅ የሚወዱን የሚያከብሩን የሚሳሱልን አንዳንዴም ከራሳቸው በላይ የሚያፈቅሩን ሰዎች ይኖራሉ።
እንደዚህ አይነት ሰዎችን አንዴ ካስቀየምናቸው መልሰን አናገኛቸውም።
ታማኝና ከልቡ ወዳጅ ሰው በጠፋበት ዘመን እንደዚህ አይነት ሰዎችን ማጣት የእድሜ ልክ ፀፀት ማትረፍ ነውና ወዳጆቻችንን ልክ እንደ ተሰባሪ እቃ በጥንቃቄ እንያዛቸው።
ይህን አንብባችሁ ስትጨርሱ ሼር ብታደርጉት ወዳጆቻችሁ ሊጠቀሙበት ይችላሉ!
Comments
Post a Comment