Posts

Showing posts from December, 2020

ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችሉ 10 ነገሮች

Image
  ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችሉ 10 ነገሮች አንዴ የተወሰነ ዕድሜ ላይ ከደረሱ የገንዘብን አስፈላጊነት ማድነቅ ይጀምራል ፡፡  እውነት ነው ገንዘብ ደስታን ሊገዛ ይችላል ግን የደህንነት ስሜት ይሰጣል።  ማንም ድሃ ለመሆን የሚጥር የለም ፡፡  እና በአሁኑ ጊዜ ሀብታም የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ያደጉ በድሃ ቤቶች ውስጥ ስለሆኑ ድህነትን እንደገና ለመለማመድ በጭራሽ አይፈልጉም ፡፡  ገንዘብ መኖሩ የሚያሳፍር ነገር አይደለም ፡፡  ገንዘብዎን ለማግኘት ጠንክረው ከሰሩ ፣ እንዴት እንደሚያወጡ የእራስዎ ነው።  ግን ትልቁ ችግር ገንዘብ ማከማቸት ቅድሚያ በሚሰጥበት ጊዜ ነው ፡፡  የበለጠ ገንዘብ ለማግኘት የሚጥሩ ሰዎች ምንም ያህል ሀብት ቢኖራቸው ፣ አሁን ካሉበት የበለጠ ደስተኛ እንደማይሆኑ በጭራሽ አይገነዘቡም ፡፡  በመድኃኒት ወይም በአልኮል ሱሰኝነት ፣ በመንፈስ ጭንቀት ወዘተ ሕይወታቸውን ያጠፉ ብዙ ታዋቂ ሰዎች አሉ እነሱ ስኬታማ እና ሀብታም ናቸው ነገር ግን በሕይወታቸው ውስጥ በቂ ደስታ አልነበራቸውም ምክንያቱም ገንዘብ ለእነሱ በጭራሽ አያስገኝላቸውም ፡፡  ገንዘብ ደስታን እንዲሁም የሚከተሉትን 10 ነገሮች በጭራሽ አይገዛም። 1. ፍቅር  ገንዘብ መስህብን ፣ ሀይልን እና ምኞትን ሊገዛ ይችላል ግን በጭራሽ አይወድም።  ፍቅር የጠበቀ ፣ ልባዊ እና ምስጢራዊ ነው ፣ ገንዘብ ግን ያን የሚያክል አይደለም።  ገንዘብ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ለመግዛት እና ምቾት እና የቅንጦት ለማቅረብ የልውውጥ ዘዴ ብቻ ነው ግን ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዳቸውም ቢሆኑ የሰው ልጅ በእውነት የሚያስፈልገው አይደለም ፡፡  ይህንን ትምህርት በከባድ መንገድ እንማራለን ፡፡...

🚺✅ ሕይወት ስትጨልምብን ✅🚹

Image
 🚺✅ ሕይወት ስትጨልምብን ✅🚹 "ሕይወት የሁለት ነገሮች ድምር ውጤት ናት ። ማግኘት አለ ማጣት አለ መወለድ አለ መሞት አለ ደስታ አለ ሀዘን አለ እንባ አለ ሳቅ አለ። ሁለቱም የህይወት አካሎች ናቸው። አንዳንዴ ህይወት እንደ ሸማኔ መወርወሪያ የሁለቱንም ጫፍ እያስነካች ትመልሰናለች። አንድ ቀን 24 ሰዓት አለው። 12ቱ ሰዓት ብርሃን 12ቱ ሰዓት ጨለማ ነው። አይ እኔ ጨለማ አልወድምና ለሊቱ ይቅርብኝ ብንል ቀናችን ጎዶሎ ነው ሚሆነው ። አንድ አመትም ክረምትና በጋ አለው። አይ ጭቃ አልወድምና ክረምቱ ይቅርብኝ ብንል አመታችንም ጎዶሎ ነው ሚሆንብን ። ስለዚህ ህይወትም ያለ ችግር ደስታውን ብቻ እንኑረው ብንል ጎዶሎ ህይወት ነው ምንኖረው። አንዳንዴ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ችግር ውስጥ የሚከተን ሕይወታችንን ሙሉ ለማድረግ ነው ። ከለሊት በኋላ ንጋት እንጂ ሌላ ሌሊት አይመጣም ። ከመከራ ቡሃላም ደስታ እንጂ ሌላ መከራ አይመጣምና ታገስ። ወዳጄ አንድ ኮኮብ ዙሪያው በጨለመ ቁጥር እሱ ይበልጥ ይበራል። ህይወትህ የጨለመብህ ይበልጥ እንድታበራ ነውና ተደሰት። እህቴ በተለያየ ሀገር በተለያየ ስራ ውስጥ እራስሽን ለመለወጥ በተለያየ አይነት ችግር ውስጥ ተወጥረሽ ይሆናል። ግን የረገበ የክራር ክር ሙዚቃ ማውጣት አይችልም። አንድ ክራር ሙዚቃ ከማውጣቱ በፊት መጀመሪያ ክሩ በደንብ መወጠር አለበት። ህይወት አንቺንም የወጠረችሽ ሚያምር ማንነትሽን ለማውጣት ነው። ወንድሜ እራስህን ለመለወጥ ስትሞክር ብዙ ነገሮች ቅጥል አርገውህ እርር ብለህ ይሆናል። ግን አስታውስ አንድ መዓዛው የሚያምር እጣን ይሸተን ዘንድ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ገብቶ መቃጠል አለበት። አንተንም ሕይወት ያቃጠለችህ ሚያምር ማንነትህ እንዲወጣ ነውና ተደሰት። ^^^^^^^^^^^"  " *አንተ...

ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች።

Image
 ትንሿ ቆንጅዬ  ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች። <<የኔ ጣፋጭ አንዱን ለኔ ለእናትሽ ትሰጪኛለሽ?>> ስትል በትህትና ትጠይቃታለች። ልጅም ትኩር ብላ ከተመለከተቻት በኋላ አንዱን አፕል ግምጥ አደረገችው...ቀጠለችና ሁለተኛውንም ደገመችው። እናት በልጇ ሁኔታ ደንግጣ ፍዝዝ ብላ ቀረች። ስሜቷን በቁጣ ልታሳያት ብትሞክርም ድንጋጤው ከለከላት። እንዴት በኔ በእናቷ ትጨክናለች? ብላ አሰበች። በዚህ መሃል  የገመጠችውን አንዱን ለእናቷ እያቀበለቻት << እንኪ ማሚ ይበልጥ የሚጣፍጠውን ላንቺ>>> አለቻት። እናት ያልጠበቀችውን ክስተት በማየቷ ልጇን አቅፋ ተንሰቅስቃ አለቀሰች። °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ቢያንስ በእያንዳንዳችን ዙርያ እኛ ምንም ሳናውቅ  የሚወዱን የሚያከብሩን  የሚሳሱልን  አንዳንዴም ከራሳቸው በላይ የሚያፈቅሩን ሰዎች ይኖራሉ። እንደዚህ አይነት ሰዎችን አንዴ ካስቀየምናቸው መልሰን አናገኛቸውም።  ታማኝና ከልቡ ወዳጅ ሰው በጠፋበት ዘመን እንደዚህ አይነት ሰዎችን ማጣት የእድሜ ልክ ፀፀት ማትረፍ ነውና  ወዳጆቻችንን ልክ እንደ ተሰባሪ እቃ በጥንቃቄ እንያዛቸው። ይህን አንብባችሁ ስትጨርሱ ሼር ብታደርጉት ወዳጆቻችሁ ሊጠቀሙበት ይችላሉ!

ልብ የሚነካ የህፃኑ ልጅ ታሪክ

Image
 ልብ የሚነካ ታሪክ ፣ ካነበቡ በኋላ ለወዳጅ ጓደኛዎ share & like በማድረግ ያካፍሉ.... ከእለታት በአንዱ ቀን ሰውዬው አዲስ መኪናውን እያጠበ፣ ቼክ ምናምን እያደረገ ነበር። የአራት አመት ሕፃን ልጁ ድንጋይ አንስቶ የመኪናውን አንድ ጎን ጫረበት። በዚህ የተናደደው አባት የልጁን እጅ ይዞ በንዴት መታው። ልጁን እየመታ የነበረው በብሎን መፍቻ መሆኑን እንኳን ልብ አላለም ነበር። አጥንቶቹ በመሰባበራቸው ልጁ የአንድ እጁን ሁሉንም ጣቶች በቀዶ ጥገና ማጣት/ማስቆረጥ እንዳለበት ሆስፒታሉ ወሰነ። ልጁ አባቱን ሲያይ . . . በጣም ስቃይ ውስጥ መሆኑን በሚናገሩ አይኖቹ እያየው «አባዬ ጣቶቼ መቼ ነው ተመልሰው የሚያድጉት?» ሲል ጠየቀው። አባት ልቡ ተሰበረ። ምንም መናገር አልቻለም። ወደ ውጪ ወጥቶ በንዴት መኪናውን ብዙ ጊዜ ደበደበው። እያለቀሰ ከመኪናው አጠገብ መሬቱ ላይ ቁጭ አለ። ቀና ሲል ህጻን ልጁ በድንጋይ የጫረውን አየ፤ ልጁ «አባዬ እወድሃለሁ» ብሎ ነበር በድንጋይ መኪናው ጎን ላይ የጻፈው። በቀጣዩ ቀን አባት እንባውን መቆጣጠር አልቻለም :( *************** *************** *************** ቁጣና ፍቅር ዳርቻ የላቸውም። ፍቅርን መርጠህ አሪፍ ሕይወት ኑር። ነገሮች ልንጠቀምባቸው፣ ሰዎች ደግሞ ልንወዳቸው ነው የተፈጠሩት። አሁን የምናየው ተቃራኒውን ነው። ሰዎችን እንጠቀምባቸዋለን - ነገሮችን እንወዳቸዋለን። ጸጸት ይገድላል። ቀስ እያለ እየገዘገዘ። ወይም ደግሞ እንደዚህ ያልታደለ አባት ራስ ለማጥፋት ይዳርጋል። የሚያስጸጽት ነገር አድርጋችሁ እንደሆን አሁኑኑ ተመለሱ። በተናደዳችሁ ወይም ባዘናችሁ ጊዜ በምትወዱት ሰው ላይ የምትወስኑትን ውሳኔ አዘግዩት። የምትፈጥሩት ሃዘን በሁዋላ ከሚገዘግዛችሁ አሁኑኑ አስተካክሉት። ደ...
Image